ሳሚኝ ቀን ይውጣልኝ መስከረሜ ይጥባ
ከፍቅርሽ ልገናኝ ከነፍስሽ ልግባባ
እንደ መላእክት ክንፍ ክንዶችሽ ይፈቱ
ዐይኖችሽ በፍቅር የኔን ይመልከቱ
ሳሚኝና ልሙት ግደዪኝ በይፋ
በመውደድሽ በኩል ወደ ጽድቅ ልጥፋ
ሳሚኝና ልሙት ነጻ አውጪኝ ግዴለም
ካንቺ በቀር ሐሳብ በአእምሮዬ ውስጥ የለም
እንግዳዬ ግባ ልቤን ውረስ በዪኝ
አያመንታ ልብሽ ፈርተሸ አትተዪኝ።
እስኪ ነፍሴን ቀርበሽ አውጊያት በሹክሹክታ
የለም ሌላ ጊዜ የለም ሌላ ቦታ።
ሳሚኝና ልሙት ግደዪኝ በይፋ
በመውደድሽ በኩል ወደ ጽድቅ ልጥፋ
ሳሚኝና ልሙት ነጻ አውጪኝ ግዴለም
ካንቺ በቀር ሐሳብ አምሮት በአእምሮዬ የለም
ሌላ ዐላውቅም እኔ
አንቺን ልወድ ነው የተለከፍኩ እኔ።
ባዶ ቀርቻለኹ
የተሰጠኹትን ባንቺ ለውጫለኹ
ፈቃድሽን መጠበቅ ልብሽ ደጅ ቆሜ
አላስብ ደግሜ ዐላውቅም ደክሜ ዐላውቅም ደክሜ
መናፈቅ ደስ ሲል!
መጠበቅ ደስ ሲል!
አንቺን የሚመስል
የወደደ እንደኔ
ይታደስ በካሳ
ኹሉን በሚያስረሣ
ጥም የእርካታን ጥልቀት እንዲያውጅ ዐውቃለኹ
ይኸው እኔም እዚህ ስጠብቅሽ አለኹ ስጠብቅሽ አለኹ
ሳሚኝና ልሙት ግደዪኝ በይፋ
በመውደድሽ በኩል ወደ ጽድቅ ልጥፋ
ሳሚኝና ልሙት ነጻ አውጪኝ ግዴለም
ካንቺ በቀር ሐሳብ በአእምሮዬ ውስጥ የለም