ገና ለገና የድሮ ፀባይ ሐሳቤ ሲቀየር
በዚህ በዚያ ነው ሐተታ ብሎ በሌላ መጠርጠር
ባያዩት እንጂ ቀማምሰው የመዋደድን ሞቅታ
ቀይሮ ድባብ - ሲጭር የልብን እልልታ
ሀ ሀ ሀ ሀ
የአዲስ ፍቅር ጣዕም ቀማምሼ
ታየሁ በደስታ እኔም ታብሼ
ሞቅ ሞቅ ያለኝ ደርሶ በእርካታ
ተጎንጭቼ ነው ልዩ ስጦታ
ደብዛዛ ነበር ልቤ ግራጫ
እስኪደማምቅ ሰው አግኝቶ አቻ
ጠፋ ተነነ ያ ቅዝቃዜ
ወዶ ተወዶ ፍቅር ሲለኮስ ጊዜ
ወዶ ተወዶ ፍቅር ሲለኮስ ጊዜ
ሀ ሀ ሀ ሀ
ከጠጅ ጠላ ልቆ የሚያርስ
ከወይን ኮኛክ ውስኪ የሚብስ
ፍቅር ነው ልቤ የቀመሰው
ለሚያውቀኝ ስካር ቢመስለው
ደብዛዛ ነበር ልቤ ግራጫ
እስኪደማምቅ ሰው አግኝቶ አቻ
ጠፋ ተነነ ያ ቅዝቃዜ
ወዶ ተወዶ ፍቅር ሲለኮስ ጊዜ
ወዶ ተወዶ ፍቅር ሲለኮስ ጊዜ